
አዳምና ሔዋን ጥፋታቸው ምንድን ነው? የአንድን ዛፍ ፍሬ መብላት የሰውን ልጅ ይኼንን ያህል ዋጋ ማስከፈል ነበረበት? እግዚኣብሔርስ ከመጀመሪያው ዛፉን ለምን ፈጠረው? ከፈጠረው በኋላስ ለምን እንዳይበሉ መከልከል ፈለገ? ከሚከለክላቸው ዛፉን ለምን አያጠፋውም? ዛፉ መልካምና ክፉን የሚያሳውቅ ዛፍ ከሆነ እግዚኣብሔር የሰው ልጆች ክፉውንና መልካሙን እንዳያውቁ ይፈልጋል ማለት ነው? አዳምና ሔዋን የዛፉን ፍሬ ሲበሉ ዓይናቸው ለምን ተከፈተ? የዕባብ ሃሳብ ልክ ነበረ ማለት ነው? እግዚኣብሔር “ከዛፉ ፍሬ በበላህ ቀን ትሞታለህ” ብሎ ተናግሮ አያለ በበሉበት ቀን ለምን ሁለቱም አልሞቱም? ሔዋን ያጠፋችው ጥፋት ምን ነበረ? አዳምስ ጥፋቱ ምንድን ነው? ሔዋን አሳሳች ተደርጋ ብዙ ትወቀሳለች፡፡ አዳምስ ንጹሕ ሰው ነበረ? በሰው ልጅ ውድቀት ላይ እባብስ ድርሻው ምንድን ነው? በእባብ ያደረው ሰይጣንስ የሰው ልጅ ከፈጣሪው ቢጣላ የሚጠቀመው ምንድን ነው? እግዚአብሔርስ ሰይጣንን ለምን ፈጠረው? ሰይጣንን ለምን ይቅር አይለውም? አለዚያም ዓለምን ከሚረብሽ ለምን ሰይጣንን ጨርሶ አያጠፋውም? እግዚአብሔር ሰውን ማዳን ሰው መሆን ለምን አስፈለገው? ሰው ላይሆን ማዳን አይችልምን?
Ships within a few days. US addresses only.